በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
-
01የኢትዮጵያ ነጋዴዎች የምክክር መድረክ አላማው
ምንድን ነው?
የዚህ መድረክ ዋነኛ አላማ በሃገራችን ያሉ የቤተሰብ ቢዝነሶችን ዘመን ተሻጋሪ ፣ ጠንካራና ተፎካካሪ እንዲሆኑ የሚያስችልና ፤ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አውድ ላይ የተመሰረተ የአመራርና አስተዳደር እውቀቶችንና ልምዶችን የሚካፈሉበት መድረክ መሆን ነው።
-
02የመድረኩ ግቦች ምንድን ናቸው?
* የሀገራችንን የቤተሰብ ቢዝነሶች በተመለከተ ቋሚ ምርምሮችን ማካሄድ ፣ የምርምሮቹን ውጤት መሰረት በማድረግ ለተለያዩ የቤተሰብ ቢዝነስ ተግዳሮቶች እንደ ተሰማሩበት ኢንዱስትሪ ሀገራዊ መፍትሄዎች የሚዳሰሱበት አመታዊ ፎረም ማዘጋጀት ፤ * አለምአቀፍ ተሞክሮዎች ላይ የተመረኮዙ ፣ በተለያዩ የቤተሰብ ቢዝነስ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑና ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚሰጡ ስልጠናዎችንና ወርክሾፖችን በተለያዩ ጊዜያት ማዘጋጀትና * እንደ አስፈላጊነቱ በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የቤተሰብ ቢዝነሶች የሚገናኙበት ፣ የሚወያዩበትና የሚመክሩበት መድረኮችን ማዘጋጀት ናቸው።
-
03ከዚህ መድረክ ዋነኛ ተጠቃሚው ማን ነው?
* መሰረታቸው ቤተሰብ የሆነ እና በንግዱ ስራ ለረዥም ጊዜ ቆይተው ስለ ንግዳቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እያሰቡ ያሉ ተቋማትና * ንግዱን ከመሰረቱት ባለቤቶች ተረክበው የንግዱን ስራ በማስቀጠል እየሰሩ ያሉ ተረካቢ ትውልዶች ናቸው።
-
04ከምክክር መድረኩ ዓላማ ጋር ተስማሚና እሴት ጨማሪ ሊሆኑ የሚችሉ አጋር
ተቋማት የትኞቹ ናቸው?
የቤተሰብ ንግድ ባለቤቶች ፣ የንግድ ስራ ትምህርት ቤቶች ፣ በቤተሰብ የንግድ ስራ ምርምር ላይ የሚሰሩ ተቋማት ፣ ከንግዱ ስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የፋይንስ ተቋማት ናቸው።
-
05የኢትዮጵያ የቤተሰብ የንግድ ስራ መድረክ አስተባባሪ እና አዘጋጅ ማን
ነው?
ኤች ኤስ ቲ ኮንሰልቲንግ ፒ ኤል ሲ የፎረሙ አዘጋጅ ሲሆን ዋነኛ የፎረሙ ተዋናዮች ግን የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት የቤተሰብ ቢዝነሶች ናቸው።