የኢትዮጵያ የቤተሰብ የንግድ ስራ ባለቤቶች መድረክ

ሀገር በቀል ከሆኑ አቻ የቤተሰብ ቢዝነሶች ጋር በመተባበርና አብሮ በመምከር ፤ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችንና ዕውቀቶችን በመቅሰምና በመተግበር ለድርጅትዎ አስተማማኝ መሰረት ይጣሉ!ስለ ፎረሙ

የቤተሰብ ቢዝነሶች አስፈላጊነት

የግሉ ዘርፍ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚጫወተው ጉልህ ሚና ላይ የቤተሰብ ቢዝነሶች ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ። ከሞላ ጎደል በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ በመሰማራት ይኸውም ለአብነት ለመጥቀስ ያህል በአስመጪና ላኪነት ፣ በኢንዱስትሪ ፣ በትምህርት፣ በግብርና ፣ በጤና ፣ በፍጆታ ዕቃዎች አቅርቦትና ስርጭት ፣ በሆቴልና ቱሪዝም ፣ በግንባታና ሌሎች እዚህ ላይ ባልተጠቀሱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ የቤተሰብ ቢዝነስ አስተዋጽኦ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። በዚህም ምክንያት የቤተሰብ ቢዝነሶች ቀጣይነትን ማረጋገጥ ማለት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሀገርን ኢኮኖሚ ማሻሻል ፣ የስራ ዕድሎችን መፍጠር ፣ ሀገርን ወደፊት የሚያራምዱና በየዘርፋቸው ፈጣን ለውጥ ማስመዝገብ የሚችሉ ተቋማትን መገንባት ነው።

በአደጉት ሀገራት የሚታዩት ተሞክሮዎችም ይህንን በግልጽ የሚያሳዩና የሚደግፉ ናቸው። መቀመጫቸውን በምዕራቡ ዓለም ያደረጉና አለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ያላቸው ፣ ዛሬ በየቤቶቻችን ምርቶቻቸውን በመደበኛነት የምንጠቀምባቸው ተቋማት አብዛኞቹ ከቤተሰብ ቢዝነስ ጎራ የሚመደቡና ለረጅም ዓመት በዘርፋቸው ላይ በመቆየት ፣ ምርቶቻቸውን ያለማቋረጥ በማሻሻልና ተወዳዳሪነታቸውን በአለም አቀፋዊ ደረጃ በማረጋገጥ የሀገራቸው ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ ቢዝነሶች ናቸው።

የቤተሰብ ቢዝነሶች በኢትዮጵያ

ይህንን ተመልክተን ወደ ሀገራችን ስንመለስ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የቤተሰብ ቢዝነሶች በተለያዩ ተግዳሮቶች ምክንያት የአቅማቸውን ያህል ሲያድጉ አይስተዋልም። ከእነዚህም ተግዳሮቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱት የአመራር ክፍተቶች ፣ ተወዳዳሪ ሆኖ መቀጠል ያለመቻል ፣ ቀጣዩ ትውልድ በተተኪነት [የቢዝነስ ባለቤቶቹ ልጆች ወይም የቅርብ ዘመዶች] ቢዝነሱን ከመሰረቱት [ከእናት ፣ ከአባት/ ከእህት ፣ ከወንድም] ተረክቦ ማስቀጠል አለመቻል ናቸው።የኢትዮጵያ የቤተሰብ የንግድ ስራ ባለቤቶች መድረክ

ከላይ የተጠቀሱትን ተግዳሮቶች በትብብር ለመፍታት እንዲያስችል ፤ ኤች ኤስ ቲ ኮንሰልቲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፤ በዓይነቱ ልዩ የሆነ “የኢትዮጵያ የቤተሰብ የንግድ ስራ ባለቤቶች መድረክ” ተብሎ የሚጠራ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል። መድረኩ ከቤተሰብ ቢዝነስ ባለቤቶች ፣ የንግድ ዘርፍ ማህበራት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና በጉዳዩ ላይ በቀጥታ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ተቋማት ጋር በትብብር እንዲካሄድ ታቅዶ የተቋቋመ ነው።

በቀጣይም ኤች ኤስ ቲ በዓመት አንድ ጊዜ መድረኩን የሚያዘጋጅ ሲሆን የማያቋርጥ ድጋፍ መስጠት እንዲያስችል የመድረኩ አባል ለሚሆኑ የቤተሰብ ቢዝነሶች ዋና በሚባሉና ለእድገታቸው ምሰሶ በሆኑ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ወርክሾፖች የሚዘጋጁ ሲሆን በየጊዜውም ተመሳሳይነት ባላቸው ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች እየተዘጋጁ የሚቀርቡና የሚሰራጩ ይሆናል።

ጽሁፍ አቅራቢዎች

ሰለሞን ግዛው


ሊቀ-መንበር እና ዋና ስራ አስፈጻሚ

ኤች ኤስ ቲ

መላኩ ከበደ


ዋና ስራ አስፈጻሚ

ህብረት ባንክ

ፓናሊስቶች

ምህረትአብ ልኡል


ማኔጂንግ ፓርትነር

ምህረትአብ እና ጌቱ አድቮኬት ኤል ኤል ፒ

ሃና ጥላሁን


ማኔጂንግ ዳይሬክትር

ቤዛል ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ ፒ ኤል ሲ እና
ሄብሮን ሪዞርት ፒ ኤል ሲ

ጸደቀ ይሁኔ


ማኔጂንግ ዳይሬክትር

ፍሊንትስቶን ኢንጅነሪንግ ኤንድ ሆምስ

ሳላሃዲን ካሊፋ


መስራች እና ስራ-አስኪያጅ

ሳማትራ ሎጂስቲክስ እና ሺፒንግ ፒ ኤል ሲ

ፕሮግራም አስተባባሪ

ዝክረ ንጋቱ


ማኔጂንግ ዳይሬክትር

ኮንሰልቲንግ እና ለርኒንግ ሶልዩሽንስ
ኤች ኤስ ቲ

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

 • 01የኢትዮጵያ ነጋዴዎች የምክክር መድረክ አላማው ምንድን ነው?

  የዚህ መድረክ ዋነኛ አላማ በሃገራችን ያሉ የቤተሰብ ቢዝነሶችን ዘመን ተሻጋሪ ፣ ጠንካራና ተፎካካሪ እንዲሆኑ የሚያስችልና ፤ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አውድ ላይ የተመሰረተ የአመራርና አስተዳደር እውቀቶችንና ልምዶችን የሚካፈሉበት መድረክ መሆን ነው።

 • * የሀገራችንን የቤተሰብ ቢዝነሶች በተመለከተ ቋሚ ምርምሮችን ማካሄድ ፣ የምርምሮቹን ውጤት መሰረት በማድረግ ለተለያዩ የቤተሰብ ቢዝነስ ተግዳሮቶች እንደ ተሰማሩበት ኢንዱስትሪ ሀገራዊ መፍትሄዎች የሚዳሰሱበት አመታዊ ፎረም ማዘጋጀት ፤

  * አለምአቀፍ ተሞክሮዎች ላይ የተመረኮዙ ፣ በተለያዩ የቤተሰብ ቢዝነስ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑና ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚሰጡ ስልጠናዎችንና ወርክሾፖችን በተለያዩ ጊዜያት ማዘጋጀትና

  * እንደ አስፈላጊነቱ በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የቤተሰብ ቢዝነሶች የሚገናኙበት ፣ የሚወያዩበትና የሚመክሩበት መድረኮችን ማዘጋጀት ናቸው።

 • * መሰረታቸው ቤተሰብ የሆነ እና በንግዱ ስራ ለረዥም ጊዜ ቆይተው ስለ ንግዳቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እያሰቡ ያሉ ተቋማትና

  * ንግዱን ከመሰረቱት ባለቤቶች ተረክበው የንግዱን ስራ በማስቀጠል እየሰሩ ያሉ ተረካቢ ትውልዶች ናቸው።

 • የቤተሰብ ንግድ ባለቤቶች ፣ የንግድ ስራ ትምህርት ቤቶች ፣ በቤተሰብ የንግድ ስራ ምርምር ላይ የሚሰሩ ተቋማት ፣ ከንግዱ ስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የፋይንስ ተቋማት ናቸው።

 • ኤች ኤስ ቲ ኮንሰልቲንግ ፒ ኤል ሲ የፎረሙ አዘጋጅ ሲሆን ዋነኛ የፎረሙ ተዋናዮች ግን የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት የቤተሰብ ቢዝነሶች ናቸው።

 

ይጎብኙን


አድራሻ:

ቦሌ ወሎ ሰፈር
ኢትዮ ቻይና ፍሬንድሺፕ መንገድ
ሚና ህንጻ 5ኛ እና 4ኛ ፎቅ

ስልክ:

+251931391100 | +251911222667
+251 (0) 11 552 7666/67